ኮፒ ራይት Disclaimer and Copyright Disclaimer:- ብሬስት ካንስርአምሃሪክ የተባለው ድህረ ገጽ የተሰራበት ዋና ዓላማ የጡት ካንሰር ምንነትን ለመረዳት ለሚፈልጉ፤ በዚህ ህመም ራሳቸው የተያዙ እና ስለበሽታው ያላቸውን ግንዛቤ ማዳበር ለሚፈልጉ፤ ላስታማሚዎችና በዚህ የህመምና ድህነት ጫና ላለባቸው ሰዎች ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልጉ ሁሉ መረጃን ለመስጠት ነው። ድህረ ገጹ ትምህርታዊ ይዘት ያለው ሲሆን ምንም አይነት የህክምና አገልግሎት ወይም የባለሙያ ምክር ለመስጠት የተዘጋጀ አይደለም። ማንኛውም የህክምና ውሳኔ ከሀኪምዎ ጋር ወይንም በራስዎ የሚያደርጉት ነገር ነው። በዚህ ድህረ ገጽ ላይ የቀረበውን መረጃ በመጠቀም ለሚደርሰው ማንኛውም አይነት የህመም መባባስ፤ ጉዳት ወይንም እክሎች እና ከህክምና ጋር የተያያዙ ጉዳቶች የድህረ ገጹ አዘጋጅ ወይንም መረጃውን በጽሁፍ በመስጠት ትብብር ያደረጉትን ቶም ቤከር ካንሰር ማዕከልን (Tom Beker Cancer Center) ወይንም www.cancer.ca በሀላፊነት የሚያስጠይቅ አይሆንም። ኮፒ ራይት Copyright:- በዚህ ድህረ ገጽ ላይ የቀረቡት መረጃዎች ከቶም ቤከር ካንሰር ማዕከልን (Tom Beker Cancer Center) ወይንም www.cancer.ca የተወሰዱ ሲሆን ለጽሁፎቹ ጥራት በቂ ጥናት የተደረገበትና የተመረጡ ናቸው። ከሌሎች ምንጮች ተገኝተው የተተረጎሙ መረጃዎች በሙሉ በባለቤትነት ያበረከቱት ድርጀርጅቶች/ሰዎች ስም ይጠቀሳሉ። ስለዚህ ከዚህ በሚከተሉት መሰረት ከድህረ ገጹ የሚያገኙትን መረጃዎች በማተም ወይንም በመገልበጥ (copy) መጠቀም ይችላሉ። 1. የትርጉም ስራውን ያገኙበትን www.weebly.breast cancer- Amharic.com በመጥቀስ። 2. ከዚህ በተጨማሪ መረጃዎቹ የተገኙበት www.cancer.ca መሆኑን በማሳወቅ። 3. ማንኛውንም በዚህ ላይ የቀረቡትን ጽሁፎች ከንግድ ጋር ላልተያያዘ ስራ በመጠቀም። 4. በቀረቡት ጽሁፎች ላይ የማሻሻል፤ የማዳበር ወይንም የመለወጥ ስራ ባለማከሄድ። የቀረቡትን መረጃዎች በድጋሚ ለመጠቀምም ሆነ ለማሰራጨት የዚህ ጽሁፍን ምንጭ በመጥቀስ ለሌሎች ግልጽ ማድረግ ይኖርብዎታል። አግባብ ያለው አጠቃቀምዎና ሌሎች መብቶችዎን ሁሉ ከዚህ በላይ በቀረበው ሁኔታ ምክንያት የሚነፈግዎት አይደለም።