ይህ ድህረ ገጽ በኢትዮጵያና በሌላው የዓለማችን ክፍል በሚኖሩ በበጎ ፈቃደኞች አስተዋጽኦ የተዘጋጀ ነው። የበጎ ፈቃደኞቹም አላማ በአለምአቀፍና በአገራችን ካንሰር የሚያስከትለውን ማህበራዊና ስነ ልቦናዊ ጉዳትን ለመቀነስና ካንሰርን ለማጥፋት ለሚካሄደውን ጥረት ውስጥ መሳተፍና እገዛ ማድረግ ነው።
በገጹ ውስጥ የሚቀርቡት መረጃዎች በካንሰር ለተያዙ ወገኖቻችን ወቅታዊ መረጃን ለማቅረብና እነሱን የሚንከባከቡ ቤተሰቦቻቸው ሊያደርጉ ስለሚገቡዋቸው ነገሮች ለማሳወቅ ይረዳሉ ብለን እናምናለን። ከዚህ በተጨማሪ ከካንሰር በሗላ ስላለው ህይወት የዳኑ ሰዎች ከካንሰር ጋር ባሳለፉት የህይወት ዘመናቸው ውስጥ ያጋጠሙዋቸውን ልምዶች፤ ያደረጉትን ጥረትና የአሁንና የወደፊት ማንነታቸውን ሊገልጹ የሚችሉበት ድህረ ገጽ ይሆናል ብለን እናምናለን። በካንሰር ህክምናና በማስታመም ላሉ ወገኖቻችን ጠቃሚ የሆኑ ሃሳቦችን ሊያካፍሉ የሚችሉ ባለሙያዎች ድጋፍ የሚሰጥ ሃሳቦቻቸውንም የሚያካፍሉበት መድረክ ይሆናል የሚል እምነት አለን። |
Acknowledgement ምስጋና
I would like to extend my complements to Mr. Loring Gimbel, Patient Education Specialist at Alberta Health Services for his unreserved advice and support in providing me with all the information I needed to develop and publish this website. From Teigist Lemma Dessalegn ይህንን ድህረ ገጽ እውን እንዲሆን ሃሳብና መረጃዎችን በመስጠት ከፍተኛ ድጋፍ ላደረጉልኝ ሚ/ር ሎሪንግ ጊምቤል ከፍተኛ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ያለእርሳቸው ድጋፍ ይህንን መረጃ ለአንባቢዎች/ተጠቃሚዎች ለማቅረብ የማይቻል ነበር። ከትዕግስት ለማ ደሳለኝ |