ጤናማ አኗኗር
በአግባቡ መመገብ (ኢት ሪይት)
በአግባቡ መመገብ ጥሩ ስሜት እንዲኖርዎትና ጥሩ ሆነው ለመታየት የሚረዳዎት መሆኑን ያውቁ ይሆናል። ሆኖም ጤናማ አመጋገብ ከአንዳንድ የካንሰር አይነቶች የመያዝ እድልዎን ሊቀንስ እንደሚችል አያውቁም ይሆናል።
የተለያየ አይነት ጤናማ ምግብ ይመገቡ
በየእለቱ እስከ አምስት ወይንም ከዛ በላይ አትክለትና ፍራፍሬ ሰርቪንግ (ሊቀርቡ የሚችሉ ወይንም አይነቶች ይመገቡ። በጣም የተጣሩ (ሪፋይንድ) ምግቦችን ከመመገብ ይልቅ ገለባቸው ያልተወገደባቸውን እህሎች መመገብ መምረጥ የተሻለ ነው።፡ቀይ ስጋ በተለይ ደግሞ ስብ/ቅባት ያላቸውና በፋክተሪ ውስጥ የተሰሩትን መመገብ ያሳንሱ።

መመገብን የሚቀንሱዋቸው ምግቦች
ፍሬንች ፍራይስ፣ የድንች ጥብስ፤ ያትክልት ጥብሳጥብሶች ጣፋጭ ምግቦች፤ ኬከች፤ ለስላሳ መጠጥ፤ ስኳር የበሬ ስጋ፤ ያሳማ ስጋ፤ የበግ ስጋ |
የሚመረጡ ምግቦች
ፍራፍሬና አትክልት ገለባቸው ያልተወገደባቸው እህሎች፤ ሩዝ፤ ዳቦ፤ ፓስታ አሳ፤ ዶሮ፤ አደንጓሬና ባቄላ ዘሮች |
ጤናማ የሰውነት ክብደት እንዲኖርዎት የሚረዳዎትን ምግብ አይነት ይምረጡ- ከቤት ውጪ በሚመገቡበት ወቅት የስብ/ቅባት ይዘታቸው፤ ካሎሪ፤ ስኳር
አነስተኛ የሆነ እና መጠኑም አነስተኛ የሆነ ይምረጡ። - የሚመገቡት ምግብ ብዙ ካሎሪ ያለው ምግብ ከሆነ መጠኑ አነስተኛ ይሁን። ስባቸው አነስተኛ ወይንም ስብ የሌላቸው ምግቦች ሁሉ ካሎሪያቸው አንሰተኛ እንዳይደለም ይገንዘቡ። ቅባታቸው አነስተኛ የሆኑ ኬኮች፤ ብሰኩቶች እና ተመሳሳይ ምግቦች አብዛኛውን ጊዜ የካሎሪ መጠናቸው ከፍተኛ ነው። - ካሎሪ የሚበዛባቸውን ምግቦች(ለምሳሌ ፍሬንች ፍራይስ የሌሎች አትክልት ጥብሳጥብስ፤ ቺዝ ያለበት በርገር፤ ፒዛ፤ አይስ ክሬም፤ ዶናቶች እና ጣፋጭ ምግቦች)በአትክልቶች፤ በፍራርሬዎች እና የካሎሪ መጠናቸው አነስተኛ በሆኑ ምግቦች ይተኩዋቸው። |
አነስተኛ ስብ/ቅባት ያላቸው ምግቦች ሃሳብ መስጫ (Tips)- ብዙ አሳ እና ዶሮ በመመገብ የቀይ የበሬ ስጋ መመገብን መቀነስ
- ቅባቱ/ስቡ ያልተወገደለት ወተት ከመጠጣት ይልቅ የስብ ይዘቱ አነስተኛ የሆነ ወይንም ስብ የሌለው ወተት መጠጣት - ቅቤ ወይንም ክሬም ያለበት መረቅ ከመጠቀም ይልቅ ቅባት የሌለው መረቅ መመገብ/መጠቀም - በቅባት ውስጥ ተነክሮ ከተጠበሰ ምግብ ይልቅ የተጋገረ፤ የተቀቀለ ወይንም በ አነስተኛ ቅባት የተጠበሰ ምግብ መመገብ - ብዙ ቅባት ያላቸውን ምግብ ሲመገቡ አነስተኛ መጠን ያለው ይሁን ብዙ ፍራፍሬና አትክልት ይመገቡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ በካንሰር የመያዝ እድልዎን በየእለቱ እስከ አምስት ሰርቪንግ (ሊቀርቡ የሚችሉ ወይንም አይነቶች) ወይንም ከዛ በላይ አትክልትና ፍራፍሬን በመመገብ መቀነስ ይችላሉ። ስለሰርቪንግ የበለጠ ለመረዳት |