ከካንሰር የሚድኑ ሰዎች ሁሉ የስሜት መረበሽ ተሞክሮ ይኖራቸዋል?
Will all cancer survivors experience emotional effects
ከካንሰር ጋር ሲኖር በስሜት ወይንም በፍላጎት (mood) ላይ የሚታይ ለውጥ የተለመደ ነው። ለምሳሌ የካንሰር ደዌ እንዳለብዎ ሲታወቅ የፍርሀት፤ የሀዘን እና ጭንቀት ስሜት ሊሰማዎት ይችላል። የህክምናዎን አይነት ከወሰኑ ብኋላ የመተማመን ስሜትዎ የተሻለ ሊሆን ይችላል። በህክምና ወቅት በስሜትዎ/ፍላጎትዎ ላይ ብዙ መለዋወጥ ሊያጋጥሞት ይችላል። ከካንሰር የዳኑ ሰዎች ይህንን አብዛኛውን ጊዜ የስሜት ነውጥ ወቅት ነው ይሉታል - አንዳንድ ቀን ጥሩ/ንቁ አንዳንድ ቀን ድግሞ ድብርት/ሀዘን ሊስማዎት ይችላል።
ብዙ ከካንሰር የዳኑ ሰዎች የካንሰር ህክምናቸው ካለቀ በኋላም በሚያጋጥማቸው የስሜት/የፍላጎት መለዋወጥ ይደነቃሉ/ይገረማሉ። ለአንዳንድ ስዎች የሚደረግላቸውን ህክምና መጨረስ የመረበሽን/የአለመደሰትን ስሜት ሊፈጥርባቸው ይችላል። ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ከካንሰር የዳኑ ስዎች እንደሚገልጹት ከሆን ህክምና ካለቀ በኋላ ያለው ጊዜ እጅግ ስሜታዊነት የበዛበት እና በህይወት ዘመናቸው ውስጥ ያላጋጠማቸው ወይንም እንግዳ የሆነ በጣም የተለየ ጊዜ ነው ይላሉ። እንደዚህ አይነት ስሜታዊ ምላሾች ከህክምና በኋላ ወደ ተለመደው ኑሮ/ሁኔታ በመመለስ ሂደት ውስጥም ሊያጋጥም ይችላል። እነዚህን ስሜቶችን መረዳት የተለያዩ ሁኔታዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ በአግባቡ ለማስተናገድና ከካንሰር ጋር መኖር የሚቻል መሆኑን ለመገንዘብና ያለንን በራስ መተማመን ለመጨመር ይረዳል።
ከዚህ በተጨማሪ ከላይ የተዘረዘሩት ሁሉም፤ ጥቂቶቹ ወይንም ምንም አይነት ስሜቶች/ስሜታዊ ምላሾች ላይታይብዎት ይችላል። የእያንዳንዱ ከካንሰር የዳነ ወይንም ከካንሰር ጋር የሚኖር ሰው ስሜትና ምላሽ የተለያየ ነው። እንደዚህ አይነት የተለያየ ስሜታዊ ምላሾች መኖራቸውን መረዳት የራስዎን የስሜት ልውውጥ ለመረዳት የሚያስችሎት ግንዛቤ እንዲኖርዎት ሊረዳዎት ይችላል።
ብዙ/በቂ መረጃን ያገኙ በዚህ ተሞክሮ ውስጥ ያለፉ ስዎች እንደሚገልጹት ከሆነ ከካንሰር ጋር የነበራቸውን ጉዞ ለመቋቋም ያገኙት መረጃ በእጅጉ እንደጠቀማቸው ይናገራሉ። የሌሎች ሰዎችን ተሞክሮ እና የተለያዩ ግንዛቤን ሊስያስጨብጡ የሚችሉ መርጃዎችን ማግኘት በተሻለ ሁኔታ ለመኖርና ሊሰማዎት የሚችሉትን ሰሜቶች ለመቀበል ጥሩ መንደርደሪያ/ጅማሬ እንዲኖርዎት ሊያደርግ ይችል ይሆናል። ለአንዳንድ ሰዎች መረጃን ማግኘት የበለጠ ሊያስጨንቃቸው የሚችል ከሆነ ጭንቀታቸው እስኪወገድላቸው ድረስ ወይንም ራሳቸውን ዝግጁ ሆኖ እስኪያገኙት ድረስ ከመረጃው መራቅ ሊጠቅማቸው ይችል ይሆናል።