ኑሮ ከካንሰር ትውውቅ በኋላ
በዚህ ስር የቀረቡት መረጃዎች ጠቅለል ያለ ለመግቢያ/መንደርደሪያ እንዲሆኑ የታሰቡ ናቸው።
አላማውም ከካንሰር ጋር እንደሚኖር ሰው ህይወትዎን ሊነካኩ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ የበለጠ እውቀት/መረጃ እንዲኖርዎት መነሻ እንዲሆንዎት እና የበለጠ ለመማር እርምጃዎችን ለመውሰድ የሚችሉባቸውን ሀሳቦች ለመስጠት ነው።
ይህ መረጃ የህክምና፤ የህግ ወይንም የገንዘብ ጉዳዮች ላይ ሙያዊ ምክር ለመስጠት ያልቀረበ እንደሆነ ተደርጎ ሊወሰድና ሊታወቅ ይገባል።
የበለጠ ለመረዳት የባለሙያ ምክር ለመውሰድ ይችላሉ።
አላማውም ከካንሰር ጋር እንደሚኖር ሰው ህይወትዎን ሊነካኩ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ የበለጠ እውቀት/መረጃ እንዲኖርዎት መነሻ እንዲሆንዎት እና የበለጠ ለመማር እርምጃዎችን ለመውሰድ የሚችሉባቸውን ሀሳቦች ለመስጠት ነው።
ይህ መረጃ የህክምና፤ የህግ ወይንም የገንዘብ ጉዳዮች ላይ ሙያዊ ምክር ለመስጠት ያልቀረበ እንደሆነ ተደርጎ ሊወሰድና ሊታወቅ ይገባል።
የበለጠ ለመረዳት የባለሙያ ምክር ለመውሰድ ይችላሉ።
ካንሰር በስሜት ላይ ያለው ተጽእኖ
Emotional Effects of Cancer
ከFacing Forward: A Guide for Cancer Survivors. National Cancer Institute, NIH Publication No. 94-2424.1-800-4-CANCER የተወሰደ።
ካንሰር በስሜት ላይ ያለው ተጽእኖ Emotional Effects of Cancer
በዚህ ስር የቀረቡት
መረጃዎች ጠቅለል ያለ ለመግቢያ/መንደርደሪያ እንዲሆኑ ታስቦ ነው። አላማውም ከካንሰር ጋር እንደሚኖር ሰው ህይወትዎን ሊነካኩ
በሚችሉ ጉዳዮች ላይ የበለጠ እውቀት/መረጃ እንዲኖርዎት መነሻ እንዲሆንዎት እና የበለጠ ለመማር እርምጃዎችን ለመውሰድ
የሚችሉባቸውን ሀሳቦች ለመስጠት ነው። ይህ መረጃ የህክምና፤ የህግ ወይንም የገንዘብ ጉዳዮች ላይ ሙያዊ ምክር ለመስጠት ያልቀረበ
እንደሆነ ተደርጎ ሊወሰድና ሊታወቅ ይገባል። የበለጠ ለመረዳት የባለሙያ ምክር ለመውሰድ ይችላሉ።
ከካንሰር ጋር መኖር አንድ የህይወት ልምድ ሲሆን በህይወትዎ ውስጥ ያለውን ሁሉ ነገርን ይነካል። ካንሰር በሰውነትዎ ላይ ከሚያስከትለው ጉዳት በተጨማሪ አእምሮዎንና መንፈስዎንም ሊጎዳ ይችላል። ለእነዚህ ለውጦችም ስሜታዊ (emotional) ምላሾች ሊኖርዎት ይችላል። የካንሰር ህክምና ካለቀ በኋላም በስሜትዎ ላይ ያለው ተጽእኖ ይቀጥላል እና አዲስ ስሜቶች ሊታይብዎ ይችላል። ከካንሰር ጋር ለመኖር ይህ ነው ተብሎ የሚታወቅ አንድ አይነት ስሜታዊ ምላሽ (emotional response) የለም። እያንዳንዱ ከካንሰር የዳነ ወይንም ከካንሰር ጋር የሚኖር ሰው የህይወት ገጠመኞቻቸው ይለያያሉ። እርስዎም ከሌሎች የተለየ ስሜታዊ ምላሾች ሊኖርዎት ይችላል እና አንዳንዶቹ አዎንታዊ ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ በጠነከረ ግንኙነትዎ/ተግባቦትዎ የረኩ ወይንም በራስዎ ውስጥ ያለውን ጥንካሬ ከመረዳት የመነጨ ያሎት በራስ መተማመን ባህሪዎ የጠነከረ/የጨመረ ሊሆን ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ አንዳንድ ስሜታዊ ምላሾችዎ የማይመቹና ግራ የሚያጋቡ ሆነው ሊያገኙዋቸው ይችላሉ። አንዳንዴ ራስዎን በሚቃረኑ ስሜትዎች ተውጠው ሊያገኙት ይችላሉ። ከካንሰር ጋር ባሎት ጉዞ ወቅት እንደዚህ የሚሰማዎት ከሆነ ይህ ስሜት በእርስዎ ላይ ብቻ የሚታይ አይደለም። ብዙ ከካንሰር ጋር የሚኖሩ ሰዎች እንደሚገልጹት ከሆነ ስሜታዊ ምላሾችን ማስተናገድ ሌሎቹን ህክምናዎች ለመቋቋም ከሚያደርጉት ጥረት ጋር ተቀራራቢ የሆነ ጥረትን፤ መረዳትን፤ ትዕግስትንና ድርጊትን ይሻል ይላሉ። |
ከካንሰር የሚድኑ ሰዎች ሁሉ የስሜት መረበሽ ተሞክሮ ይኖራቸዋል?
|
Life after cancer ሕይወት ከካንሰር በሗላ
ሕክምናዎ አልቋል። ከካንሰር በሗላ ሰላሎት ህይወት ደስተኛነት፤ ተነሳሽነትና ስጋት ባንድ ላይ ባንድ ጊዜ ተቀላቅለው ሊሰማዎት ይችላል።
I’m a survivor ካንሰርን የተቋቋምኩ ነኝ
ካንሰርን ተፋጥጠው “የተቋቋሙት” ወይንም ሌሎች ይህንን መሰል ሀረግ/ቃል ሲነገር ሰምተው ይሆናል። ሀረጉ/ቃሉ ምን ማለት ነው? ለተለያዩ ሰዎች የተለያየ ትርጉም ሊሰጥ ይችላል። የቃሉን/ሀረጉን አጠቃቀም አይወዱት ይሆናል ወይንም እርስዎን የሚመለከትዎት ላይመስልዎት ይችላል። ሆኖም የተቋቋሙ የሚለው ቃል ብዙ ሰዎችን ይረዳል። ቃሉ/ሀረጉ ብርቱና አዎንታዊ ገጽታ አለው። ለአንዳንድ ሰዎች ራሳቸውን በጥሩ ሁኔታ እንዲገነዘቡትና ቀና አመለካከት እንዲኖራቸው ይረዳል። ቃሉን/ሀረጉን መጠቀም ከካንሰር በሗላ ያላቸውን ሁኔታ እንዲከታተሉትና እንዲቆጣጠሩት ይረዳቸዋል።
The end of treatment የህክምና ማብቃት
በህክምና ወቅት ህክምናው ያልቃል ብሎ ማሰብና መገመት አስቸጋሪ ይሆን ይሆናል። ምናልባት እርስዎና ቤተሰብዎ የሳለፋችሁት እያንዳንዷን ቀን በመቁጠር ሊሆን ይችላል።
እርስዎም ብዙውን ጊዜዎን ከህክምና በሗላ ያለውን ጊዜ እያሰቡ ሊሆን ይችላል ያሳለፉት። አሁን ደግሞ ከህክምናው በፊት የነበሩበትን ሁኔታ እያሰቡ ከእዛጋ መጀመር እችል ይሆን ብለው ያሰላስሉ ይሆናል። አሁን ጊዜው ወደ ተለመደው ሁኔታ የመመለስና ጥሩ ሁኔታ (መጪ ጊዜ) እንደሚያጋጥሞት እያሰቡ ደስታ የሚሰማዎት ጊዜ ነው። ነገር ግን ከካንሰር ህክምና በሗላ ያለው ጥሩ ሁነታ (normal)ማለት ምን ማለት ነው?
The new normal አዲሱ ጥሩ ሁኔታ
የሁሉም የካንሰር ህክምና ጉዞ/ልምድ የተለያያ እንደመሆኑ መጠን ከካንሰር በሗላ ካለው ህይወት ጋር መለማመድም እንዲሁ ከሰው ሰው ይለያያል።
ለአንዳንድ ሰዎች፤ ከካንሰር ጋር ያላቸው ልምድ ቀይሮኛል ብለው እንደሚያስቡት መጠን፤ አዲስ ጥሩ ሁኔታ ማለት ሙሉ በሙሉ ቀድሞ ወደ ነበሩበት ህይወት መመለስ ሊመስላቸው ይችላል። ለእነዚህ ሰዎች ህክምናውን የመጨረስ ጥሩነቱ ወደ ተለመደው የእለት ተግባራቸውና አሰራራቸው መመለስ ማለት ነው።
ለሌሎች ሰዎች ደግሞ እንደዚህ ቀላል ላይሆን ይችላል። ህመም ካሁን በሗላ ላይሰማቸው ይችላል። ሆኖም ራሳቸውን ቀደሞ (ከህክምና በፊት) እንደሚሰማቸው ሆነው ላያኙት ይችላሉ።
የተለያዩ አካላዊና የኑሮ ሁኔታዎች (practical issues) ጋር የተያያዙ (አዲስ የጤና ሁኔታና የገንዘብ ጉዳይ) የአሁኑ ህይወትዎ ዋነኛ አካል ሆነው ሊያገኙት ይችላሉ። ያሎትም ማህበራዊ እሴቶችና ቀዳሚ ጉዳዮችዎ (priorities) ከቢፊቱ ለውጥ ሊኖራቸው ይችላል። ከቤተሰብና ከጓደኞችዎ ጋር ጊዜን እንደማሳለፍ ወይንም የሚወዱትን ነገር በማድረግ ጊዜዎን እንደማጥፋት የንብረት/ቁሳቁስ ጉዳዮች ብዙ ግድ ላይልዎት ወይንም ስሜት የማይሰጥዎት ሊሆኑ ይችላሉ።
ሌላው ከላይ በተጠቀሱት ስሜቶች መካከል ሆነው ራስዎን ሊያገኙት ይችላሉ። በአንዳንድ የህይወት ጉዳዮች ላይ አዲሱ ሁኔታ በጣም የተለየ ሆኖና በሌሎች ሁኔታዎች ደግሞ እንደቀድሞው ሆኖ ሊያገኙት ይችላሉ። አንዱ ሁኔታ/መንገድ ከሌላኛው የተሻለ ነው ማለት አይደለም። ሆኖም ዋናው ነገር ለእርስዎ የተሻለውንና ጥሩ የሚሆነውን ለይቶ ማወቅ ነው።