ህክምናዎን ከጨረሱ በኋላ የሚሰማዎት የተደበላለቀ ስሜት እና ወደ ቀድሞው የኑሮ የመመለስ ሂደትዎ ከዚህ
የሚከተሉትን ጨምሮ በብዙ ምክንያቶች የተነሳ የተለየ/የሚደንቆት/የሚገርሞት ሊሆን ይችላል።
- ከካንሰር ጋር ባሳለፉት ልምድ ውስጥ ያላስትዋሉት/ያላወቁት ስሜት ሊታይብዎ ይችላል። እስከእዚህ ጊዜ ድረስ ጉልበትዎን/ትኩረትዎን ያጋጠሞትን ያልተለመደ የህክምና ሁኔታን ለመወጣት ሲሞክሩ ቆይተው ይሆናል። ምናልባት ትኩርትዎ ጥሩ የህክምና ቡድን ማግኘት፤ የተሻለ የህክምና ዘዴን መምረጥና ህክምናውን ማጠናቀቅ ሆኖ ሊሆን ይችላል። ትኩረትዎን ከካንሰሩ ጋር ተያይዘው ሊመጡ የሚችሉትን የስሜት ለውጦች ከመከታተል አስወግደው ከሆነ ይህ አይነቱ ሁኔታ ሊያጋጥሞት ይችላል።
- ምናልባት ከካንሰሩ ጋር በመኖርዎ ምክንያት በስሜትዎ ላይ ሊመጣ የሚችለውን ተጽዕኖ ለማስተናገድ ሳይዘጋጁ ቀርተው ሊሆን ይችላል። ካንሰር ሊያስከትል ስለሚችለው አካላዊና ከኑሮ ጋር ስለተያያዘው ችግርና የሆናሉ ተብለው ስለሚገመቱት ነገሮች ብዙ ሰምተው/አድምጣው እና አንብበው ሊሆን ይችላል። ነገር
ግን ካንሰር በስሜት ላይ ሊያመጣ ስለሚችለው ለውጥ/ሁኔታ ብዙ በመስማት/በማድመጥ እና በማንበብ መረጃ ላያገኙ ይችላሉ። ብዙ ጊዜ በጣም አስፈላጊ በሆኑ ከካንሰር ህክምናና አብሮት ከመኖር ጋር የተያያዙ ውይይቶች/ጽሁፎች ውስጥ በስሜት ላይ ስለሚያመጣው ተጓዳኝ ለውጦች/ችግሮች ሳይዳሰሱ ይታለፋል።
በአካባቢዎ ያሉ ሰዎች ህክምናን መጨረስ በስሜትዎ ላይ ሊያደርግ የሚችለውን ተጽዕኖ ላይረዱት ይችላሉ። የቤተሰብ አባላት፤ ጓደኞች እና የህክምና ቡድንዎ ህክምና መጨረስዎን እና ካንሰርን ድል ያደረጉ መኖኑን ሊያከብሩ ተዘጋጅተው ሊሆን ይችላል። ወደ ቀድሞ ሁኔታዎ ተመልሰው ኑሮዎን የሚጀምሩ ሊመስላቸው ይችላል። ሌሎች የእርስዎን ድል አድራጊነትንና ስኬታማ መሆንዎን በሚያከብሩበት ወቀት የራስዎን የሀዘንና የፍርሀት ስሜት መረዳት/መቀበል(acknowledging) አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።